አመራሩና ማህበረሰቡ ለቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ትኩረት እንዲሰጥ ተጠየቀ።

በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትን ለማጠናከር የንቅናቄ መድረክ ተጠናቋል።
የእናቶችን ጤና በማሻሻል እና ብሩህ ትውል ለማፍራት የረዥምና አጭር ጊዜ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ በጤና ቢሮ የእናቶች ህፃናትና ሥርዓተ ምግብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሪሁን ገብሬ እና የኃይለማሪያምና ሮማን ፋውዴሽን ስኔ-ተዋልዶ የእናቶችና ህፃናት ጤና ከፍተኛ ባለሙያ ዶ/ር አብርሃም አላኖ በሰነዳቸው አስደምጠዋል።
ለእናቶች የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትን እስከ ታች ድረስ ለማድረስ ከዚህ በበለጠ በመስራት የተቀናጀ ጤናማ የቤተሰብ አገልግሎት ማስፋፋት እንደሚገባ የዞንና ወረዳ አስተዳዳሪዎች በአስተያየት ተደምጠዋል።
በዕቅድ የሚመራ ቤተሰብ በማጠናከር ሴቶች በወንዶች የሚደርስባቸውን ጫና ለማስቀረት ሁሉም ማህበራዊ መሰረቶች ሊያግዙአቸው እንደሚገባ ጤና መምሪያና ጽ/ቤት ኃላፊዎች ተናግረዋል።
ከዩኒቪርሲቲ ተወክለው የመጡ ከፍተኛ አመራሮች በበኩላቸው በቤተሰብ ዕቅድ ዙሪያ ጥናትና ምርምሮችን በማካሄድ የማህበረሰብ ቁርኝነትና ግንዛቤን በማጠናከር ማህበረሰቡን ለማገልገል መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።
የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና አብያቴ ክርስቲያናት ህብረት ጋር በመተባበር ለማህበረሰቡ በዘርፉ ግንዛቤ ለመፍጠርና አላስፈላጊ እሳቤዎችን ለማስቀረት እንደሚሰሩ አስተያየት ሰጥተዋል።
የጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና ህክምና አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ናፍቆት ብርሃኑ በበኩላቸው፤ ቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት አለመጠቀም ላልተፈለገ እርግዝና ስለሚዳርግ ጥንቃቄ ያሻል ብለዋል።
አንድ እናት ስትጠነክር ማህበረሰብ ይጠነክራል፥ ማህበረሰብ ስጠነክር ሀገር ይጠነክራል! ያሉት የኃይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክብርት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ፤ ለእናቶች ጤና እና ቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ሁላችንም ልንረባረብ ይገባል ብለዋል።
ከፍተኛ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ችግር ያለባቸው ወረዳዎችን ለይተው በመስራት የተሻሻለ አገልግሎት ማየት መቻላቸውን ወ/ሮ ሮማን አስረድተዋል።
በመጨረሻም የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ እንዳሻው ሽብሩ እንደተናገሩት ከጤና ኬላ ጀምሮ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎቱን አቀናጅቶ ለተሻለ ለውጥ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
የማህበረሰብ ተሳትፎን በማጠናከር በማህበረሰቡ የሚነገሩ ሀሰተኛ እሳቤዎችን ለማስቀረት የሀይማኖት አባቶች አደራቸውን ሊወጡ ይገባልም ብለዋል።
ቢሮ ኃላፊው ጨምረው፥ የተለያዩ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትን ለእናቶች ተደራሽ በማድረግ ጤናቸው የተሻሻለ ቤተሰብና ማህበረሰብ መፍጠር ይገባናል ብለዋል።
የዞንና ወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎች፣ጤና መምሪያና ጤ/ጽ/ቤት ኃላፊዎችን ጨምሮ ሁሉም የመድረኩ ተሳታፊዎች የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ተጠቃሚነትን ማጠናከር ይገባል ሲሉ ቢሮ ኃላፊው እንዳሻው ሽብሩ አሳስበዋል።
ሐምሌ 11/2018
ጤና ቢሮ ኮሚኒኬሽን