#ጣናችን | የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት የክልል ላቦራቶሪዎች የአራት ወራት የሥራ አፈጻጸም ተገመገመ።
ሕዳር 18/2019 ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት
___________
የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በድሉ ቁጮ በመድረኩ እንደተናገሩት በክልሉ በሚገኙት ሁለቱ የሕብረተሰብ ጤና ላቦራቶሪዎች የአቅም ግንባታና የአገልግሎት ማሻሻያ ሥራዎች ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።
የጂንካ እና የአርባምንጭ ሪጅናል ላቦራቶሪ ኃላፊዎች አቶ ሀብታሙ ከተማ እና አቶ ከበደ ሙልሳ በበኩላቸው በአራቱ ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን አቅርበዋል።
በተለያዩ የጤና ተቋማት የቫይራል ሎድ ምርመራ የሚከናወንባቸው ተቋማት ቁጥር ወደ 75 መድረሱን በሪፖርቱ ተገልጿል።
ከፀረ ተሕዋስያን መድኃኒት መቋቋም ጋር በተያያዘ ያሉ ሥራዎችን በማከናወን የሁለቱ ላቦራቶሪዎችን በሙሉ አቅም ወደ ሥራ ማስገባት፣ የተመረጡ ተቋማትን መደገፍና የክትትል ሥርዓቱን ማጠናከር እንደሚገባ ተነግሯል።
ኢንስቲትዩቱ በመጠናከሩ ለሕብረተሰቡ የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ጥራት ከፍ እንደሚያደርግ አቶ ከበደ ሙልሳ በአስተያየታቸው ጠቁመዋል።
ከፍተኛ የላቦራቶሪ ባለሙያ አቶ መርሁን ዳዊት ከፀረ ተሕዋስያን መድኃኒት መቋቋም ጋር በተያያዘ የተመረጡ የጤና ተቋማትን በተገቢው ሁኔታ መደገፍና የክትትል ሥራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ምንተስኖት መልካ በበኩላቸው ሁለቱም ላቦራቶሪዎች እኩል የሥራ አቅምና ኃላፊነት ያላቸው በመሆናቸው በትብብርና ቅንጅት መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በድሉ ቁጮ በማጠቃለያቸው ላቦራቶሪው ልምድና የሥራ ዕውቀት እንዳላቸው ገልፀወ‍እ፤ ላቦራቶሪዎቹን ለማጠናከር የሚያስችል መዋቅር፣ የሰለጠነ ባለሙያዎችን ማብቃት ያስፈልጋል ብለዋል።
ተቋማቱ ሙሉ አቅም በመጠቀም የምርምር ሥራዎች ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል፣ ክፍተቶችን በማሻሻልና ለሥራው የሚረዱ አጋር አካላትን በማፈላለግ የላቦራቶሪዎቹን አቅም ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የላቦራቶሪዎቹን የሥራ አፈጻጸም ለመገምገም፣ ያሉ ክፍተቶችን ለይቶ ለማሻሻልና የክልሉን የሕብረተሰብ ጤና ላቦራቶሪ አገልግሎት ጥራት ለማሳደግ ያለመ መድረክ መሆኑም ታውቋል።
#ጤና_ቢሮ

See less