የወባና ስርዓተ ምግብ አለመመጣጠን በሽታን የመከላከል ተግባራት በሁሉም መዋቅሮች ተጠናክሮ እንዲቀጥል የክልሉ ጤና ቢሮና ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት አስታወቀ።
ነሐሴ 22/2018 ጤና ቢሮ ኮሚኒኬሽን | ጂንካ
___________
በሳምንቱ 5ኛ ቀን የIMS ሪፖርት ያቀረቡት አቶ በአይቸው ሙላቱ ሰኢሆኑ፤ በተደረጉ ቅንጅታዊ ተግባራት የወባ በሽታ ጫና እየቀነሰ መምጣቱን በሪፖርት አስደምጧል።
በየደረጃው የተካሄደው የቤት ለቤት በሽታ ቅኝትና አሰሳ ሥራ አበረታች ለውጥ ያሳየ መሆኑንም በመጠቆም።
የስርዓተ ምግብ አለመመጣጠን በሽታ ያለባቸዉ ወረዳዎች በድንገተኛ ክስተት አስተዳደር ግብረኃይል በመደገፍ ከዚህ ቀደም ተደራሽ ያልሆኑ ህጻናትን ማግኘት ማስቻሉ ተብራርቷል።
የIMS ትግበራ የተዘረጋባቸውና ያልተዘረጋባቸው የጤና ተቋማት ንቁና ዝግጁ በመሆን ለዜጎች ጤና መሻሻል መስራት እንዳለባቸው አቶ ዋዱ ማርሻሎ ገልጸዋል።
የጤናና ጤና ነክ ቁጥጥር በሳምንቱ የተጠናከረ ሲሆን፤ ከህገወጥ ተግባራትን የሚከላከል ማህበረሰብ ማጠናከር ይገባልም ተብሏል።
ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ምክትል ዳይሬክተር አቶ አሳምነው አይዛ በበኩላቸው ከIMS ትግበራ ውጪ ባሉ ወረዳዎች ላይ ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
በሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መልካሙ ቶንቼ፤ ውሃ ማከሚያ አኳታብ በመጠቀም የተጀመረው ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ምንተስኖት መልካ የተወሳሰበ የስርዓተ ምግብ አለመመጣጠን በሽታን በመከላከል፤ ልዩ ትኩረት በሚሹ አካባቢዎች ትኩረት ማድረግ ይገባል ብለዋል።
ዶ/ር ምንተስኖት ጨምረው በዞን ደረጃ የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት እና ዝቅተኛ አፈጻጸም የሚታይባቸው አከባቢዎችን በመደገፍ የማህበረሰብ ተሳትፎ በተመረጡ ወረዳዎች እና ሌሎች አከባቢዎች ላይ ማጠናከር ይገባል ብለዋል።








