ሕዳር 16/2019 ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት
_________
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ደሣለኝ የወረርሽኞች መስፋፋትን ለመከላከልና የክትባት አገልግሎት ለማሻሻል የጤና ኤክስተንሽን ፕሮግራም መደገፍ እንደሚገባ ገለፁ፡፡
የክትባት ቅዝቃዜ ሰንሰለት ክትትልን በማጠናከር ክትባቱን ለሁሉም ህፃናት ተደራሽ ለማድረግ መሥራት እንደሚገባም ቢሮ ኃላፊው አሳስበዋል፡፡
በክትባት መከላል የሚቻሉ በሽታዎችን በመከላከል የህፃናትን ጤና ማሻሻል እንደሚገባ ምክትል ቢሮ ኃላፊና ጤና ፕሮግራም ዘርፍ ኃላፊ ናፍቆት ብርሃኑ ተናገሩ፡፡
በመድረኩ የእናቶችና ህፃናት ጤናና ሥርዓተ ምግብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መርሁን ገብረ 1ኛ ሩብ ዓመት ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
በሪፖርቱ በቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ራስን በራስ በመቆጣጠር እና ሥነ ተዋልዶ አገልግሎችን በማስፋት ወደ ህብረተሰቡ በመውረድ ክትትል ማድረግ እንደሚገባም በመጠቆም፡፡
በቢሮ የክትባት አማካሪ አቶ ተካልኝ ሣህለ የክትባት ማካካሻ አገልግሎት ትግበራ ሰነድ አቅርበዋል።
በመድረኩ የክልሉ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች፣ ማናጅመንት አባላት፣ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊዎች፣ የዞን እናቶችና ህፃናት ጤናና ሥርዓተ ምግብ አገልግሎት ዳይሬክተሮች፣ አጋር ድርቶች፣ ክትባት አማካሪዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡










