በጤናው ሴክተር የሪፎርም ግቦችን ውጤታማ ለማድረግ ቅንጅታዊ አሰራሮች ሊጠናከሩ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ እንዳሻው ሽብሩ አስታወቁ።
ሪፎርሙን ከንድፈ-ሀሳብ ባሻገር ውጤታማ እንዲሆን ቅንጅታዊ አሰራሮች ሊጠናከሩ እንደሚገባም ቢሮ ኃላፊው አሳስበዋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ እንዳሻው ሽብሩ እንዳሳሰቡት ሪፎርሙ ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ 2 ዓመት ወዲህ የህፃናትና እናቶች ሞት በእጅጉ መቀነሱን አብራርተዋል።
በጥራት፣ ፈጠራ እና ከወረቀት ነፃ አሰራር ስርዓት በመዘርጋት የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ፣ የወረቀት አገልግሎትን በሂደት የማስቀረት ሥራ ልጠናከር ይገባልም ብለዋል።
ሪፎርሙ የህክምና መረጃዎች ፍሰት፣ ፈጣንና ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ እንዲሆንና የታካሚዎችን የህክምና ቆይታ ጊዜን ለመቀነስ እንደሚያግዝ ተነግሯል።
የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች እንደ ሀገር በዘርፍ ለተመዘገበው ተጨባጭ ለውጦች የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ መሆናቸውን ቢሮ ኃላፊው አብራርተዋል።
በጤና ሚኒስትር የሚኒስቴር ዴኤታው ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር ያሬድ አግደው በበኩላቸው፤ ሪፎርሙ አክሞ የማዳን አገልግሎትን መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል፡፡
የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በፌዴራልና ክልል የተጀመረው ሪፎርም እስከታችኛው ዞንና ወረዳ መዋቅር እንዲወርድና አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግ ጠይቀዋል።
የቀረቡ ሰነዶች ከአስተማርነታቸው በላይ ወደ ተግባር ከተቀየሩ ከሀገር እስከ ማህበረሰብ እና ጤና ሴክተር ለውጥ አዘል መሳሪያ እንደሆነ ተሳታፊዎች በአስተያየታቸው ተደምጠዋል።
በስልጠናው የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ እንዳሻው ሽብሩ፣ ጤና ቢሮ ምክትሎች፣ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊዎችና ምክትሎች፣ የዩኒቨርሲቲ ተወካዮች፣ የቢሮ ተጠሪ ተቋማት፣ የጤና ቢሮ ማናመንት አካላት፣ ከጤና ኤክስቴንሽን እስከ ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪሞች በሙያ ስብጥር የመድረኩ ተሳታፊዎች ተግኝተዋል፡፡
በመጨረሻም የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የማጠቃለያ መዕክት በዲጂታል አውታሬ መረብ ሰጥተው ስልጠናው ተጠናቋል።




