የጤና መረጃዎችን ፈጣን፣ ጥራት ያለው እና ዲጂታል ለማድረግ ትግበራውን ማጠናከር እንደሚገባም የድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር ማዕከል አስታውቋል።
ጥቅምት 16/2019 ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት
__________
የትንኝ መራቢያ ቦታዎችን ማጽዳት እና በየጤና ተቋማት በቂ የህክምና አቅርቦትና ምርመራ ማረጋገጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በድሉ ቁጮ አሳስበዋል።
ቅድመ ጥንቃቄዎችን፣ የበሽታ ስርጭት ቁጥጥርን እና የሃብት ድልድልን በመረጃ ላይ ተመስርቶ ለመወሰን ሁሉም በትጋትና መተባበር መስራት ይገባልም ብለዋል።
ለወባ መከላከልና ምላሽ ስራዎች የአልጋ አጎበር ድልድል እና የቤት ውስጥ ፀረወባ ኬሚካል ርጭትን እና አከባቢ ቁጥጥር ማጠናከር እንደሚገባም በሪፖርቱ ተብራርቷል።
የክፍኝ ወረርሽኝ ምላሽ ስራ የመደበኛና የድንገተኛ ክትባት ሽፋንን በማሳደግ የወረርሽኝ ስርጭትን መግታት እንደሚገባም ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር በድሉ አስታውቀዋል።
የኢቦላ ቅድመ መከላከልና ለቁጥጥሩ ትኩረት በመስጠት ቀሪ ተግባራትና ቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በየደረጃው ማጠናከር እንደሚገባ የኢንስትቲዩቱ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ምንተስኖት መልካ አስታውቀዋል።
በድንበርና የፍተሻ ጣቢያዎች ላይ የጉዞና የጤና ምርመራና ፍተሻ ቁጥጥርን ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በድሉ ቁጮ አሳስበዋል።


