የአጋር ድርጅቶች ድጋፍና ቅንጅታዊ አሰራ ለጤና ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮና ህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት ድህረ ማርበርግ ቫይረስ በሽታ ቅኝት ሥራዎችን ተመለክተዋል፡፡

በመድረኩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አጉኔ አሾሌ እንዳስታወቁት ክልሉ በተቀናጀ ሁኔታ ወረርሽኙን መቆጣጠር መቻላቸውን ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት አስታውሰዋል፡፡
ለወረርሽኙ ቁጥጥር መላው ሀገር በንቃት የተባበረ ሲሆን፤ አጋር ድርጅቶች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ጤና ባለሙያዎች፣ ባለድርሻ አካላት እና በህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ክልላችን መቆጣጠር ችሏል፡፡
ህብረተሰቡን በልዩ ልዩ ቋቋዎች ግንዛቤ በመፍጠር፣ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በሚዲያ ማሰራጨት፣ ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁና ግንዛቤ ተፈጥሮ ውጤት መመዝገቡ በሪፖርቱ ተደምጧል፡፡
የተለያዩ አጋር ድርጅቶች የቁሳቁስ፣ የገንዘብ ድጋፍ እና ግንዛቤ ሥራ እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች ርብርብና የህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ወረርሽኙ እንዳይስፋፋ መቆጣጠር ተችሏልም ብለዋል፡፡
ማርበርግ ወረርሽኙን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ በሽታዎች፣ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን፣ የእንሰሳት በሽታ ክስተት እንደ ክልል የታዩ ችግሮች እንደ ነበሩ በውይይቱ ቀርቧል፡፡
የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝን መቆጣጠር መቻል፣ ድንበር ተሸጋሪ በሽታ ቁጥጥር ሂደት፣ ከመረጃ አያያዝና ስርጭት አንፃር እና ለዜጎች ተገቢውን የህክምና እርዳታ ከመስጠት አንፃር የነበሩ ተግዳሮቶችን አጋር ድርጅቶቹ ጠይቀዋል፡፡
ክልሉ ጠንካራ የቀውስ ክስተት አስተዳደር ስርዓት ግብረኃይል ማቋቋም በመቻሉ፣ የበሽታ ቅኝትና ቁጥጥር ቡድን በማሰማራቱ፣ ያልተቆራረጠ የመረጃ ስጭት ተደራሽ ማድረጉ፣ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በቅርበት መስራቱ እና ጠንካራ የጤና ባለሙያዎች ርብርብ ውጤታማ እንዳደረጋቸው የክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አጉኔ አሾሌ አስታውቀዋል፡፡
በበርካታ የህክምና ተቋማት የውሃ ችግር መኖሩን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ክልሉ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ቢመሆንም ድጋፍ ያሻል ብለዋል፡፡
የክልል ምርምርና ህክምና ላቦራቶሪ ክልሉ ካለው ስፋት አንፃር ለህብረተሰቡ የተሻለ የህክምናና ጤና ሥርዓት መስራት እንዲቻል ድጋፍ ይገባል ብለዋል፡፡
በጤና ተቋማት የተሻለ የህክምና አገልግሎት መስጠትና የጤና ኤክስተንሽን ፕሮግራምን በማጠናከር እየተሰራ ቢሆንም ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ተግባራት ናቸው ሲሉ ምክትል ቢሮ ኃላፊና ህክምና አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ናፍቆት ብርሃኑ ጠይቀዋል፡፡
የክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ምንተስኖት መልካ በበኩላቸው፤ በተደራጀና ጠንካራ የህብረተሰብ ጤና ቁጥጥርና መከላከል ሥርዓት በመዘርጋቱት ወረርሽኙን መቆጣጠር መቻሉን አብራርተዋል፡፡
በክልሉ የህብረተሰቡን ጤና የህክምና ዋስትናነን ለማረጋገጥ በቅንጅት መስራትና ድጋፍ እንደሚያስፈልግ የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት የድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር ከፍተኛ ባለሙያ አቶ አስራት ቦሻ ጠይቋል።
በክልሉ ‹‹ዞኖቲክ ዲዚዝ›› ከሰው ወደ እንሰሳት እና ከእንሰሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች መኖራቸውንም አቶ አስራት አስረድተዋል፡፡
በመጨረሻም ከማርበርግ ወረርሽኝ ክስተት ጊዜ ጀምሮ ድጋፍ ያደረጉና ድህረ ማርበርግ ኩኔትን ምልከታ ያደረጉ ባለድርሻ አካላትን የክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አጉኔ አሾሌ በጤና ቢሮ ስም አመስግነዋል፡፡
መጋቢት 23/2018 ዓ.ም
ጤና ቢሮ ኮሚኒኬሽን ዳሬክቶሬት
ጂንካ
May be an image of one or more people and textMay be an image of one or more people, table and text that says 'የደቡ ኢትዮዽያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ h Ethiopi EthiopiRegionalState Regional State Healt HealtBureau Bureau'