የተቀናጀ ፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በጌዴኦ ዞን በይፋ ተጀመረ
‎
‎በዞኑ ከ258 ሽህ በላይ ህጻናት የሚከተቡበት 3ኛ ዙር የተቀናጀ ፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በጌዴኦ ዞን በይፋ ተጀምሯል።
‎
‎በዞን ሁሉም መዋቀር ተግባራዊ በሚደረገው 3ኛ ዙር የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) ክትባት በዞኑ 258 ሽህ 568 በላይ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት እንደሚከተቡ የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ ገልጿል።
‎
‎መምሪያዉ ዞን አቀፍ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የፌዴራል የክልልና የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በዲላ ዙሪያ ወረዳ ቱምትቻ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ላይ በይፋ አስጀምረዋል።
‎
‎በመርሀግብሩ ላይ የተገኙት የኢፌዲሪ የጤና ሚኒስቴር ተወካይ ዶክተር ጉልላት ገዛኸኝ ባስተላለፉት መልዕክት ተላላፊ የሆኑ በሸታዎን መከላከል መንግስት ትኩረት ሰጥተው እየሰራ ካለዉ ስራ አንዱ መሆኑን ገልጿል።
‎
‎የፖሊዮ በሽታ ክትባት የዚህም ስራ አንዱ አካል መሆኑን አብራርተዉ ለዕቅዱ መሳካት ወላጆችና አሳዳጊዎች እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆናቸው ህጻናት መከላከያ ክትባት እንዲወስዱ በማድረግ በሽታው ከሚያስከትለው ጫና ቀድመው መከላከል እንዲችሉ በማድረግ ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፏል።
‎
‎የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፖለቲካና የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ አየለ ፖሊዮ (የልጅነት ልምሻ) ከ5 ዓመት በታች የሆኑትን ህጻናት የእግርና እጅ ነርቮችን የሚያጠቃ፣ መንቀሳቀስ እንዳይችሉ የሚያደርግ መድኃኒት የለለው በክትባት ብቻ መከላከል የሚቻል ተላላፊ በሽታ መሆኑን በመገንዘብ ወላጆች/አሳዳጊዎች ህጻናት ማስከተብ እንደሚገባ አሳስበዋል።
‎
‎የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አንዱአለም ማሞ የፖሊዮ በሽታ በሀገር ደረጃ ለማጥፋት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን በመግለጽ ከክትባት ዘመቻው ጎን ለጎን መደበኛ ክትባት ያልወሰዱ እና ክትባት ወስደው ያቋረጡ ህፃናትን የመለየት ስራ እንደሚሰራም ተናግረዋል።
‎
‎በተጨማሪም ከወሊድ ጋር ተያይዞ የፊስቱላ ችግር የገጠማቸውን እናቶች የመለየትና ህክምና የመስጠት ስራ እንደሚሰራም አቶ አንዱአለም አስታውቀዋል።
‎
‎እንዲሁም የሥርዓተ-ምግብ ችግር ያለባቸዉን ህፃናት፣ ነፍሰ-ጡር እና አጥቢ እናቶች በመለየት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንደሚደረግ ተገልጿል።
‎
‎የዲላ ዙሪያ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊና የወረዳዉ ም/አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ቦኮ መንግስት ሁሉም ዜጋ ጤናው የተጠበቀና ማህበራዊ ብልጽግና የተረጋገጠ እንዲሆን በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።
‎
‎ክትባቱ ከዛሬ መስከረም 30/2018 እስከ ጥቅምት 3/2018 ቤት ለቤት ለ4 ተከታታይ ቀናት ቤትለቤት በዘመቻ የሚሰጥ መሆኑን ተመላክቷል።
‎
‎@የጌዴኦ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን