የጤና መረጃ አስተዳደር፣ ጥናት ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር የ2018 በጀት ዓመት የዘርፍ ሥራ አፈፃፀም መመልከቱን የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት አስታወቀ።
የኢንስትቲዩቱ ምክትል ዳይሬክተርና የጤና መረጃ አስተዳደር፣ ጥናት ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ አሳምነው አይዛ እንዳስታወቁት የምርምር ሥራዎች ማጠናከር ለጤና ስርዓት ግንባታ ወሳኝ መነሻ ናቸው ብለዋል።
ውይይቱ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ አበይት ተግባራት፣ የተመዘገቡ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በመድረኩ የ2019 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ላይም ምክክር ተደርጎበታል።
በ2018 በጀት ዓመት በጥንካሬ የተከናወኑ ተግባራትን በዝርዝር የተመለከቱ ሲሆን፣ መልካም ተሞክሮዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል የሚያስች አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
በተጨማሪም የታዩ ጉድለቶችንና ክፍተቶችን በቀጣይ ለማረም የሚያስችሉ ስልቶች ላይ የጋራ መግባባት ተፈጥሯል።
ምርምር ዘርፉ በቀጣዩ የ2019 በጀት ዓመት ትኩረት ሰጥቶ ሊንቀሳቀስባቸው በሚገቡ ጠቋሚ ዕቅዶች ዙሪያ በስፋት መክሯል።
የጤና መረጃ አስተዳደርን ማዘመን፣ ጥናትና ምርምርን ማስፋፋት እና የጤናውን ዘርፍ ውጤታማነት ለማረጋገጥ የምርምር ሥራው በትኩረት ሊሰራበት ይገባልም ብለዋል።



