የወባ በሽታን ለመከላከል ቤት ለቤት የምደረገው የጉብኝትና የአሰሳ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር ማዕከል አስታወቀ።
ነሐሴ 06/2018 ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዪት | ጂንካ
____________
የወባና ስርዓተ ምግብ አለመመጣጠን በሽታ ቁጥጥር ወረዳዎች በተቋቋመው የIMS ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አጉኔ አሾሌ አስታወቁ።
ከአከባቢ ቁጥጥር አንጻር ወባ በየአከባቢው ጥሩ አፈጻጸም የተመዘገበ ሲሆን፤ አንዳንድ ወረዳዎችን በመደገፍ የዜጎችን ጤና ማጠናከር እንደሚገባ አቶ አብርሃም ሞጋ ወቅታዊ ሪፖርት ተደምጧል።
የወባን በሽታን መርምሮ ከማግኘት አንጻር ያለውን ምጣኔ ለማሳደግ የላቦራቶሪ ጥራት ስራ አጠናክሮ መሰራት እንዳለበት የህክምና አገልግሎት ከፍተኛ ባለሙያ ዶ/ር አካሉ አደፋ ተናግረዋል።
ተጠያቂነትን በማስፋት እና የቁጥጥር ስራን በማጠናከር የሰው ልጆችን ጤና ልጎዱ ከሚችሉ መዲሃኒቶች የህብረተሰቡን ጤና እንዳይጎዱ ተባብሮ መስራት እንደሚገባ የህክምና ጥራት ቁጥጥር ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ፍሳኔ ፍርዳ ናቸው።
የህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ምክትል ዳይሬክተር አቶ አሳምነው አይዛ በበኩላቸው የንቅናቄው ስራ እስከ ማህበረሰቡ በማድረስ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ይገባል ብለዋል።
በሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ዳይሬክተር አቶ መልካሙ ተንቼ ወባ እና የስርዓተ ምግብ አለመመጣጠን በሽታን ለመከላከል እተሰራ ያለውን ስራ አበረታች በመሆኑ ክትትሉን ማጠናከር እንደምገባ ጠቁመዋል።
የህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አጉኔ አሾሌ በበኩላቸው በሳምንት እና በየቀኑ የሚመጡ ጤና መረጃዎች በማደራጀት ለህብረተሰብ ጤና ክልላዊ የጤና ተግባራትን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
የሥርዐተ ምግብ አገልግሎት በሽታ ችግር ያለባቸው የህፃናት ህክምና ማዕከል የሌላቸው ዞኖች በቀጣይ ተግባዊ እንዲያደርጉ አቶ አጉኔ አሳስበዋል።
የህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አጉኔ አሾሌ ጨምረው የወባ ቁጥጥር ተግባሩ በታቀደው መሠረት ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን አስታውቀዋል።







