የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ቢሮ ጋር በመተባበር 26ኛ ሳምንት የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል ግምገማ ማካሄዱን አስታውቋል ።
በግምገማው በትኩረት ከተነሱ ነጥቦች፤ በዞኖች ደረጃ በየሳምንቱ ግምገማውን ማስቀጠልና ለዉሳኔ መጠቀም ፤የሪፖርት ወቅታዊነትና ሙሉነት ፤ የሥርዓተ-ምግብ እጥረት ሁኔታና ህክምና ፤ የእናቶችና የጨቅላ ህጻናት ሞት ሪፖርትና የምላሽ ተግባራት ፤ የኤችአይቪ በሽታ ቅኝትና የምላሽ መስጠት ተግባራት፤ የድንገተኛ አደጋዎች ሪፖርት ለማዘመንና ለማሳለጥ እንደ ክልል እየተተገበረ ያለዉ ሲስተም የደረሰበት ሁኔታ፤ የወባ በሽታ ስርጭትና ለመቆጣጠር የተሰሩ ተግባራት፤ ኤም ፖክስ (Mpox) ሁኔታና የቅኝትና አሰሳ ሥራ በዝርዝር ተገምግሞ ፤ የመፍትሔ አቅጣጫና የድርጊት መርሐግብር ተቀምጧል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ም/ኃላፊና የፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ መና መኩሪያ የወባ በሽታ ስርጭቱን ለመቆጣጠር በከፍተኛ ጫና በተለዩ መዋቅሮች የአጎበር ስርጭትና የፀረ-ወባ ትንሽ ቤት ለቤት የኬሚካል ርጭት የተጀመረው ስሆን አፈፃፀሙን መከታተል እና ጎን ለጎን በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚሰሩ ተግባራትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ በአጽንኦት አንስተዋል።
በተጨማሪም የተወሳሰበ የሥርዓተ-ምግብ እጥረት ለመቅረፍ በቅንጅት መሰራት እንዳለበትም አቶ መና አሳስቧል::
አቶ መና አያይዘውም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በተለይም የደም ግፊት እና የስኳር በሽታ ለመከላከል በየሳምንቱ ሪፖርት የሚደረገውን መረጃ ለዉሳኔ በመጠቀም መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አጉኔ አሾሌ በበኩላቸው መረጃ ማዘመን ልዪ ትኩረት የተሰጠው ተግባር ስለሆነ ወደኋላ የቀሩ መዋቅሮች ላይ ልዩ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አስገንዝቧል።
ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም እንደ ክልል የኤምፕክስ(የዝንጀሮ ፈንጣጣ ) ቅኝትና አሰሳ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ፤ በየጊዜው የተጠረጠሩ ሰዎች ናሙና ምርመራ ተደርጎ በሁሉም ላይ እንዳልተገኘ ፤ እና እንደ ክልል እስከአሁን በሽታ ያለበት ህሙማን እንዳልተገኘና ህብረተሰቡ ሳይረበሽ ከጤና ቢሮ እና ከእንስቲትዩቱ የሚሰጠውን ምክረ ሀሳብ መተግበር እንዳለባቸው አንስተዋል ። እንደ ክልል እየተሰራ ባለው ቅኝትና አሰሳ በሽታው ከተገኘ ለይቶ ለማከም ሆስፒታሎችን ጨምሮ ሌሎች ጤና ተቋማት ዝግጁ መሆናቸውን አንስተዋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና ዘርፈ ብዙ ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጣር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ጋርሾ በበኩላቸዉ የኤችአይቪ በሽታ ልየታ በሁሉም አከባቢ ተጋላጭነት መለየትና ምርመራ ማድረግ ፤ በሽታ የተገኘባቸው ሰዎች ህክምና ማስጀመር ወጥ በሆነ ሁኔታ መሰራት እንዳለበት አንስተዋል
የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ምንተስኖት መልካ በሰጡት አስተያየት አሁን ላይ ያለዉን የወባ በሽታ ስርጭት ለመግታት የአጎበር ስርጭትና የፀረ-ወባ ትንሽ ኬሚካል ርጭት መጀመሩ እጅግ በጣም ወሳኝ ስለሆነ አፈጻጸሙን መከታተል፤ ቤት ለቤት የተሰራጨውን አጎበር አጠቃቀም መከታተል በልዩ ትኩረት መሰራት እንዳለበት አንስተዋል።
በዉይይቱ ላይ የክልሉ ህብርሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከል አባላት ፣ ከፍተኛ ባለሙያዎች ፤ የተለያዩ አጋር ድርጅቶች በተገኙበት ግምገማ በማካሄድ ፤ የቀጣይ ድርጊት መርሐግብር በማዉጣት ተጠናቅቋል።
የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ጂንካ
Points raised in focus in the assessment; to continue the assessment every week at zonal level and use it for decision; the currentity and completeness of the report; the status of malnutrition and treatment; the death of maternal and infant reports and response activities; the situation of the system being implemented as a region to update and update emergency reports; the spread and control of malaria. Works done; Mpox situation and coordination work reviewed in detail; solution direction and action plan is set.The deputy head of the Southern Ethiopia Regional Health Bureau and the head of the programs sector Mr. Mena Mekuria has emphasized that in order to control the spread of malaria, the chemical spraying of small house to house has been started and we need to monitor the implementation and strengthen the activities that work side by side with community participation.In addition, Mr. Mena stressed that to solve the complex food shortage, it should be done in harmony.Mr. Mena Ayayizewum has said that to prevent non communicable diseases, especially hypertension and diabetes, he should use the information reported every week for decision making.The director of the Southern Ethiopia Regional Institute of Public Health Mr. Agune Ashole has made him realize that updating information is something that is focused on, special support is needed on the structures that are left behind.The Director General doesn’t know that as a region, the MPS (monkey flakes) is being done carefully, that the samples of suspected people have been tested and not found on all of them, and as a region, no patients with disease have been found and that they should follow the advice given by the health office and the institute without disturbing the society. According to the regional rehabilitation and research, other health institutions including hospitals are ready to treat the disease.Deputy head of the regional health bureau and the head of multiple sectors of HIV AIDS prevention and control Mr. Mathewos Garsho has done the HIV testing and identifying all around the area. He has pointed out that starting treatment for people with the disease should be done regularly.According to Mr. Mintesnot Melka, the vice director of the regional Institute of Public Health, in order to prevent the spread of malaria, it is very important to monitor the performance and to monitor the use of malaria spreads from house to house should be paid with special attention.During the discussion, the regional public health emergency coordination center members, senior experts, and various partner organizations have conducted an evaluation and the next action plan was concluded.The regional institute of public healthጂнка




