#ጤናችን የጤናው ሴክተር ሪፎርም ተቋማዊ አሠራሮችን የሚያዘመንና የሚያሻሽል የለውጥ መሣሪያ ነው፤ ጤና ቢሮ
የጤና ቢሮ ሪፎርም ኮሚቴው የዕቅድ ዝግጅቱን እና ትግበራ ምዕራፍ ሪፖርቱን በማናጅመንት አስገምግሟል፡፡
ጥቅምት 18/2019 ጤና ቢሮ ኮሚኒኬሽን
———————
ቴክኖሎጂን በመጠቀም፣ ብቃት ያለው ሠራተኛን በማብቃትና የተሻለ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለመስጠት ሪፎርም ሥራን አጠናክሮ እየሠራ መሆኑን ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡
ቢሮ ኃላፊው አቶ ዳዊት ደሣለኝ የአፈፃፀም አመላካች ቁልፎችን ተግባራዊ በማድረግ የሪፎርም ዕቅድ ዝግጅትና ትግበራ ድረስ ያሉ ዝግጅቶች ተጠናክረው እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡
ሪፎርሙ ዘጠኝ አምዶች ያሉት ሲሆን፤ ቀልጣፋና ተደራሽ የመንግስት አገልግሎት አቅርቦት ሥርዓትን በመዘርጋት ለሠራተኞችንና ተገልጋዮችን ምቹ የሥራ አከባቢ ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን ኮሚቴው አመላክቷል፡፡
የመንግሥት ሠራተኞች የብቃት ምዘና ማረጋገጫ ሥርዓት መገንባት፣ ዲጂታል ሲቪል ሰርቪስ አሠራርን በማጠናከር፣ የወረቀት አልባ ሥራን ማሳለጥ፣ ብዝኋነትና አካታችነት ያረጋገጠ ሲቪል ሰርቪስ ተቋም ለመገንባት እየተሰራ ነው፡፡
ለአላማ የቆመ ነፃና ገለልተኛ ባለሙያ፣ የባለሙያ የሥራ መዘርዝር፣ የሰው ኃይል ስምርትና ቅንጅትን ለማሳለጥ ሪፎርሙ ታሣቢ ተደርጎ እየተሰራ መሆኑም አስተያየት ተሰጥቷል፡፡
በየዳይሬክቶሬቱ የሰው ኃይል ጉድለቶችን ታሳቢ ያደረገ ሪፎርም እንዲሰራ የተናገሩት የሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በድሉ ቁጮ፤ የተቋሙን የሥራ ቅልጥፍና ለማሻሻል የሚያግዝ ሪፎርም እንዲሠራ አስገንዝበዋል፡፡
ምክትል ቢሮ ኃላፊና ጤና ፕሮግራም ዘርፍ ኃላፊ ናፍቆት ብርሃኑ በበኩላቸው ከወረቀት ንክኪ ነፃ ዲጂታል አሠራሮችን እስከ ታችኛው መዋቅር ተጠናክሮ መስራት የሚያስችል ሪፎርም እንዲሠራ አስታውቀዋል፡፡
የጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ደሣለኝ፤ ብቁና የተደራጀ የሰው ኃይል በማብቃት ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት እና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እንዲያደረግ ሪፎርሙ በፍጥነትና ጥራት እንዲሰራ አስገንዝበዋል፡፡
የርፎርም ዕቅድና ትግበራውን በጊዜ ሰሌዳ በመከፋፈል ጊዜንና ሀብትን በመቆጠብ ሥራውን በፍጥነት ለውጤት ማብቃት ይገባል ብለወዋል አቶ ዳዊት፡፡
ከጤና ሚኒስቴር ጀምሮ ያለውን የአደረጃጀት ሥርዓትን በመከተል የሪፎርም ጥናት ቡድኑ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩቱን በጥናቱ አካቶ እንዲሰራ ቢሮ ኃላፊው አቶ ዳዊት ደሣለኝ አሳስበዋል፡፡

#ጤና_ቢሮ

See less