በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞንና ዲላ ሪጅዮ ፖሊስ ከ258 ሺህ በላይ ዕድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህጻናት ሶስተኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ይሰጣል—— አቶ አጉኔ አሾሌ
በክልሉ ጌዴኦ ዞንና ዲላ ሪጅዮ ፖሊስ ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 03/2018 ዓ/ም ለተከታታይ 04 ቀናት የሚሰጠውን የሶስተኛ ዙር የተቀናጅ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ አስመልከቶ መግለጫ ሰጥቷል::
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የሕበረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬከተር አቶ አጉኔ አሾሌ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ 258,568 ህፃናት የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 03/2018 ዓ/ም ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቅቆ ነጌ በይፋ እንደሚጀምር ገልፀዋል።
በዘመቻው ወቅት የጤና ባለሙያዎች፣ የሴቶች ልማት ህብረት፣ የትምህርት ተቋማት ፣የሃይማኖት ተቋማት ፣ የሚዲያ አካላት እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ለክትባት ዘመቻው ስኬታማነት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
አቶ አጉኔ አክለዉም ከዚህ ዘመቻ ጋር ተቀናጅቶ በመደበኛ ክትባት ያልወሰዱ ህፃናትንና በተለያዩ ምክንያት ክትባት ጀምረው ያቋረጡትን በመለየት ክትባቱን እንዲያገኙ ማድረግ ፣ የህፃናትና ነፍሰ ጡር እናቶች የሥርዓተ-ምግብ ደረጃ ሊየታ ማድረግና ችግር ያለበቸውን የህክምና አገልግሎት መስጠት እንዲሁም ፣ከወሊድ ጋር ተያይዘዉ የሚከሰት ፊስቱላ ያለባቸዉ እናቶችን በመለየት የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ በትኩረት መሰራት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።
በጌዴኦ ዞንና በዲላ ሪጅዮፖሊስ በሁሉም አካባቢዎች የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ በጥራትና በጥንቃቄ ተደራሽ ለማድረግ ግብዓትን ጨምሮ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ በየደረጃዉ የሚገኘው አመራርና ባለድርሻ አካላት ለተግባሩ ባለቤት ሆነዉ በቅንጅት በመስራት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት