የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አጉኔ አሾሌ አዲሱን 2018 ዓ/ም አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
ዋና ዳይሬከተሩ በመልዕክታቸው ለመላው ለክልላችን እድሁም ለሀገራችን ህዝቦች አዲሱ 2018 ዓመት የሰላም፣ የደስታ እና የጤና እንዲሆን ተመኝተዋል ።
ኢንስትቲዩቱ የህብረተሰቡን ጤና ለማሻሻል በሳይንሳዊ መረጃ ላይ በተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥ፣ በቴክኖሎጅ ሽግግር፣ ውጤታማ በሆነ የድንገተኛ የህብረተሰብ የጤና ችግር መከላከል፣ ቁጥጥር እና እንዲሁም የላቀ ጥራቱ የተረጋገጠ የህክምና ላቦራቶሪ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን በአድሱ በጀት ዓመት ለድንገተኛ አደጋዎች የማይበገር የጤና ሥርዓት በመፍጠር የሕብረተሰቡን ጤና በተሻለ ደረጃ ለማሻሻል ተግቶ ይሰራል፡፡
የዘንድሮውን አዲስ ዓመት ለየት የሚያደርገው እንደ ሀገር፣ በሁሉም ዘርፍ በርካታ ድሎችና ስኬታማ ስራዎች የተመዘገበበት የማንሰራራት ዘመን እንደነበርም እንዲሁም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እውን ሆኖ መመረቁና የሉአላዊነታችን ማረጋገጫ የባንዲራችን ፕሮጀክት በመሆኑ ነው ብለዋል ።
በመጨረሻም የአዲስ ዓመት በዓልን ሲናከብር የተቸገሩትን በመጠየቅ ፣ የተራቡትን በማብላት ፣ የተጠሙትን በማጠጣት ፣ በመተጋገዝ እና ጎን ለጎን ራሳችንና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን ከተላላፊና ተላልፊ ካልሆኑ በሽታዎች በመጠበቅ ሊሆን እንደሚገባ በመግለፅ አዲሱ ዓመት ፣ የፍቅር ፣ የአንድነት ፣ የአብሮነትና የብልጽግና እንዲሆን ተመኝተዋል።
አቶ አጉኔ አሾሌ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር