በሚቀጥሉት 10 ቀናት የዝናብ ስርጭቱ ለክረምት ዝናብ ተጠቃሚዎች የግብርና ሥራ አዎንታዊ ሚና ቢኖረውን የሚቲዎሮሎጂ ምክረ ሀሳቦችን ገቢራዊ ማድረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ፡፡
ኢንስቲትዩቱ ከነሐሴ 5 ቀን 2017 ጀምሮ ባሉት 20 ቀናት ያለው የአየር ሁኔታና በግብርና እንቅስቃሴ ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ተፅዕኖ በተመለከተ ለኢዜአ በላከው መግለጫ አብራርቷል።
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በመግለጫው፤ ባለፉት 10 ቀናት በ108 የሀገሪቱ አካባቢዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚሊ ሜትር በላይ የሆነ ከባድ ዝናብ መጣሉን አስታውሷል፡፡
ከነሐሴ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት አስር ቀናት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ይበልጥ ተጠናከረው እንደሚቀጥሉ አስታውቋል።
በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ መካከለኛው፣ ምሥራቅና ሰሜን ምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተሻለ የዝናብ መጠንና ስርጭት ይኖራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል፡፡
ይሄንን ተከትሎ የሚኖረው የእርጥበት ለወቅቱ የግብርና ሥራ እንቅስቃሴ በአመዛኙ አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው በመግለጫው ተብራርቷል፡፡
ይሁን እንጂ ተያያዥ ስጋቶችን ለመቀነስ እና የሚኖሩ መልካም አጋጣሚዎችን ለላቀ ሁኔታ ለመጠቀም የቀረቡትን ቦታ ተኮር የሚቲዎሮሎጂ ምክረ ሀሳቦች በአግባቡ መተግበር እንደሚገባም አሳስቧል፡፡
በእርጥበታማው የአየር ሁኔታ በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምሥራቅ፣ ምሥራቅና መካከለኛው የዝናቡን ስርጭት መስፋፋት ተከትሎ ከመካከለኛ እስከ ከባድ ዝናብ ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በዚህም በውሃ አካላት እና በከባቢ አየር ውሰጥ ከሚጠናከሩ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በመነሳት በመካከለኛው፣ በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን መስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች በ24 ሰዓት ውሰጥ ከ30 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል በትንበያው ተገልጿል፡፡
በአብዛኛው የክረምት ተጠቃሚ ተፋሰሶች ላይ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ መጠን ያለው የገጸ ምድር ውሃ ፍሰት እንደሚኖር በመግለጽ፤ አልፎ አልፎ ቅጽበታዊ ጎርፍ እና በወንዞች ከፍታ መጨመር በታችኛው ተፋሰሶች ላይ የወንዞች መጥለቅለቅ ሊከሰት ይችላል ብሏል፡፡
ከነሐሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት አስር ቀናት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ሲሆን፤ አልፎ አልፎ በረዶ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ለወንዞች መሙላት አስተዋጽኦ ሊያደረግ ይችላል ተብሏል፡፡
በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፡ ሰሜን እና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ ሊከሰት እንደሚችል በመግለጽ፤ የሚቲዎሮሎጂ ምክረ ሀሳቦች በአግባቡ መተግበር እንደሚገባ አሳስቧል ሲል የዘገበው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ነው፡፡
The Ethiopian Meteorological Institute warned that even though the rain has a positive impact on agriculture, caution should be taken.The Ethiopian Meteorological Institute has warned that if the rain spreads will have a positive role for the winter rain users, it is necessary to fund meteorological suggestions.The institute has explained in a press release to EZEA regarding the impact of the weather in the 20 days starting from August 5, 2017.Ethiopian Meteorological Institute in its statement, in the last 10 days, in 108 areas of the country, it has rained more than 30 millimeter in 24 hours.From August 5, 2017 E. It has been announced that the meteorological aspects that will create a comfortable situation for winter rains will continue to be strengthened in the last ten days.It has been stated that in the southwest, west, northwest, north, middle, east and north east areas of the country better rainfall rate and distribution is expected.It is explained in the statement that the humidity that is following this will have a positive role in the current agricultural activities.It is said that in order to reduce the associated concerns and utilize the good opportunities that exist, it is necessary to implement the location oriented meteorological suggestions.In the wet weather, moderate to heavy rainfall is expected in the west, northwest, northeast, east and central.Due to the strong meteorological aspects of water and surrounding air, the forecast has stated that there is a possibility of heavy rainfall of more than 30 millimeters within 24 hours in the middle, west, north west, northeast areas of the country.According to the fact that there will be low to high level surface water flow on most winter use streams; occasional flash flooding and rising river elevations may cause flooding in lower streams.From August 12, 2017 E. The meteorological aspects of rainfall will continue to be strengthened in the last ten days. It is said that occasional heavy rain mixed with ice may contribute to the filling of rivers.The Ethiopian news service has reported that there is a possibility of heavy rainfall in the west, north west, northern and central areas of the country and that meteorological advices should be implemented properly.