በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ሃይሉ የተመራ ልዑክ አርባምንጭ ከተማ ገባ።

በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ሃይሉ የተመራ ልዑክ አርባምንጭ ከተማ ገብቷል።
‎ልዕኩ አርባምንጭ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አጉኔ አሾሌ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ምተንስኖት መልካሙን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ልዑኩ በቆይታው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ተግባራት እና የህብረተሰብ ጤና ላቦራቶሪ ያለበትን ደረጃ የሚጎበኝ ይሆናል።
A delegation led by Dr. Mesay Hailu, the director of Ethiopian Public Health Institute has arrived in Arbaminch city.
A delegation led by Dr. Mesay Hailu, the director of Ethiopian Public Health Institute has arrived in Arbaminch.
When the delegation arrived at Arbaminch International Airport, the head of the Southern Ethiopia Regional Health Bureau Mr. Endashaw Shibru, the director of the Southern Ethiopian Public Health Institute Mr. Agune Ashole, the deputy director of the Southern Ethiopia Public Health Institute, Mr. Mitensnot Melkamun and the vice director of the region welcomed them.
During his stay the delegation will visit the state of emergency response and social health laboratory in southern Ethiopia.