የሕዝብን ጤና ለመጠበቅና ለማሻሻል የሚያስችሉ ሁሉን አቀፍ አገልግሎቶች ጤናማ እና አምራች ዜጋ ለማፍራት ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ

የበሽታ ወረርሽኝ እና የጤና አደጋዎችን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባም ተመላክቷል
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2017 በጀት አመት ዓመታዊ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ በአርባምንጭ ከተማ አካሂደዋል ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ በመድረኩ ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት የሕዝብን ጤና ለመጠበቅና ለማሻሻል የሚያስችሉ ሁሉን አቀፍ አገልግሎቶች ጤናማ እና አምራች ዜጋ ለማፍራት ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ገልፀዋል ።
የበሽታ ወረርሽች እና የጤና አደጋዎችን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ስርጭትን እና ቀደምት ማስጠንቀቂያን ማጠናከር: በጤና ስጋቶች ላይ መረጃ በመሰብሰብ እና መተንተን ህብረተሰቡን በፍጥነት ለማስጠንቀቅ እንደሚረዳም ተናግረዋል ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አጉኔ አሾሌ በበኩላቸውተቋሙ የጤና ሥርዓትን ለማጠናከርና የሕዝቡን ጤና ለመጠበቅ የሚያስችሉ ሰፋፊ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ እንደሚገኝ አስታዉቋል።
የጤና ምርምሮችን በማካሄድ፣ በሽታዎችን በመቆጣጠር፣ የላብራቶሪ አገልግሎቶችን በማሻሻል እንዲሁም ለሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ በመስጠት ረገድ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ መሆኑንም አመላክተዋል።
በጤና ስጋቶች ላይ መረጃን የመሰብሰብ፣ የመተንተን እና የማሰራጨት ስራዎችን በፍጥነት እና በትክክል መረጃዎችን ማግኘት ወረርሽኝን ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት የሚመለከታቸው አካላት ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ያስችላልም ብለዋል።
በቀጣይም ቅንጅታዊ አሰራሮችን አጠናክሮ በመቀጠል የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ በትኩረት መስራት እንደሚገባም ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል ።
የመደድረኩ ተሳታፊዎችም ባለፍው በጀት አመት በርካታ ወረርሽኞች የተከሰቱበትና መቆጣጣር የተቻለበት መሆኑን ጠቁመው ከወባ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ያሉ ክስተቶች አሁንም ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።
አያይዘውም በቀጣይም የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከአጎበር ስርጭት፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ጨምሮ የእናቶች ማቆያን ከማስፋፋት ጋር ተያይዞ የክልሉ ጤና ቢሮ ትኩረት እንዲያደርግ ጠይቀዋል ።
ከቤቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ከመድረክ ምላሽና ማብራርያ ተሰጥቶታል ።
It has been stated that comprehensive services to protect and improve the health of the people have an important role in producing healthy and productive citizens.
It has been proven that there should be a lot of attention to prevent and respond to disease epidemic and health accidents.
The Southern Ethiopian Regional Institute of Public Health has held the 2017 fiscal year annual performance review forum in Arbaminch city.
The head of the Southern Ethiopia Regional Health Bureau Mr. Endashaw Shibru in the summary message of the stage stated that comprehensive services that can improve and protect the health of the people have an important role in producing healthy and productive citizens.
They said that to prevent and respond to disease epidemics and health accidents, there should be a lot of attention.
Strengthening dissemination and early warning: Collecting and analyzing information on health concerns will help to warn the society quickly.
The director of the Southern Ethiopia Regional Institute of Public Health Mr. Agune Ashole has announced that the institute is providing a wide range of services to strengthen the health system and protect the health of the people.
They have indicated that it is playing a key role in conducting health tests, controlling diseases, improving laboratory services and responding to public health emergencies.
They have said that collecting, analyzing and disseminating information on health risks and getting information quickly and accurately information will enable the concerned authorities to prepare to prevent and respond to the epidemic.
The Director General stressed that we should continue to strengthen coordinated procedures and work carefully to protect the health of the community.
The participants of the conference also pointed out that many epidemics happened in the last fiscal year and that it could be controlled. Special attention should be given to the events related to the plague.
They have asked the regional health bureau to pay attention to prevent and control the epidemics that will happen in the future from spreading agober, awareness raising activities and expanding maternity wards.
Answers and explanations have been given to the questions raised from the house.