የለዉጡ መንግስት የጤናው ዘርፍ ስብራትን ለመጠገን አዲስ የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ ወደ ስራ አስገብቷል – ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ፍኖተ ካርታ አፈፃፀም ላይ የአመራርና የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ንቅናቄ የማጠቃለያ መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የንቅናቄ መድረኩ “የጤና ኤክቴንሽን ፕሮግራም ለሁሉ አቀፍ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት የደም ስር ነው” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ መቆየቱ ታዉቋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ባለፉት የለዉጥ አመታት የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በመደመር መንገድ ስኬቶችን አስመዝግበናል ብለዋል።
በተለይም ማህበራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የነበሩ ማነቆዎችን በመፍታት በጤና ፍትሃዊነት፣ ጥራትና ተደራሽነት ላይ ለዉጥ መምጣቱን ተናግረዋል።
የለዉጡ መንግስት የማህበራዊ ስብራትን ለመጠገን ሪፎርም ሲያደርግ ጤናን ተደራሽና ጥራት ያለዉ አገልግሎት መስጠት ለተጀመረው የብልጽግና ትልም ወሳኝ መሆኑን በማመን እንሆነም ጠቅሰዋል።
አዲስ የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀትም ማወያየት፣ ማብቃትና ማስገንዘብ የሪፎርሙ አካል በማድረግ ተግባራዊ ማድረጉን ጠቁመዋል።
በክልሉ በሚገኙ 1 ሺ 400 ቀበሌያት መሠረታዊ የጤና አገልግሎቶች ተደራሽ እንዲሆኑ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ እንደነበርም አፅንኦት ሰጥተዋል።
ክልሉ የሰላም፣ የልማትና የብልጽግና ተምሳሌት እንዲሆን የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች እያበረከቱ ላለዉ አስተዋጽኦም ምስጋና አቅርበዋል።
የጤና ባለሙያዎች በርካታ ጥያቄዎች እንዳሉባቸው ቢታወቅም ስራቸዉን በማከናወን ጥያቄያቸውን በህጋዊ መንገድ ላቀረቡ የጤና ባለሙያዎች የክልሉ መንግስት እዉቅና ይሰጣል ብለዋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ከፍተኛ መሻሻል መጥቷል ብለዋል።
በ 1996 ዓ.ም ተግባራዊ በተደረገው ፕሮግራም በቤተሰብ ዕቅድ፣ እናቶችና ህፃናት ሞት እንዲሁም የቲቢ ልየታ እመርታዊ ለዉጥ መመዝገቡንም አስረድተዋል።
እየተቀዛቀዘ የመጣውን የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም በአዲስ መልክ ወደ ስራ ለማስገባትም የቀጣይ 15 ዓመት የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቀዋል።
በንቅናቄዉ የማጠቃለያ መርሃ ግብር የክልሉ ፓርቲና መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የጤና ቢሮና የህብረተሰብ ጤና ሳይንስ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የጤና ኤክቴንሽን ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

The reformed government has prepared a new health extension roadmap to fix the brokenness in the health sector and put it into operation – President Tilahun Kebede

The Southern Ethiopia Region Health Extension Program Roadmap Implementation of Leadership and Health Extension Professionals Movement is underway in Arbaminch city.
It is known that the platform of the movement has been held under the slogan “Health extension program for comprehensive health services is the root of our blood”.
The president of the South Ethiopia region Mr. Tilahun Kebede has said that in the past years of change we have achieved success in ensuring the overall prosperity of our country.
They have said that there is change in health justice, quality and access by solving the barriers that were meant to ensure social prosperity.
While the reformed government reformed to fix the social fracture, they believed that giving health access and quality services is important for the development worm.
They have pointed out that they have made a new health extension roadmap and discussed, empowering and raising awareness as part of the reform.
They have emphasized that the role of health extension professionals was important to make basic health services available in the 1 thousand 400 kebeleys in the region.
They have thanked the health extension professionals for their contribution to make the region a symbol of peace, development and prosperity.
Even though it is known that health professionals have many questions, the regional government has said that it will give recognition to those health professionals who have done their work and presented their questions legally.
The head of the regional health bureau Mr. Endashaw Shibru said that there has been a huge improvement in the health extension program in the past two decades.
In 1996 E.C. In the program implemented, they explained that there is a change in family planning, mothers and children death and TB identification.
In order to bring the health extension program that is getting cold, they have announced that the health extension roadmap has been prepared for the next 15 years.
The regional party and government senior officials, health bureau and public health science leaders and experts and health extension experts were present at the closing program of the movement.