የሁለተኛ ዙር የተቀናጀ ክልላዊ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሄደ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የሁለተኛ ዙር የተቀናጀ ክልላዊ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በደቡብ ኦሞ ዞን በማሌ ወረዳ በኮይቤ ማዕከል በይፋ ተጀምሯል።
የማሌ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ አልጋጋ ባልንሴ በስፍራዉ በመገኘት ለእንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፊ የፖሊዮ ዘመቻ በሀገራችን ብሎም በአለም መንግስታት በሽታዉን ለመግታት ወጥ የሆነ አቋሚ መኖሩንም አንስቷል።
ይህን ዘመቻ ከግብ ለማድረስ እንደ ወረዳ 21,000 ሺህ ህፃናቶችን ለማስከተብ ማቀዱንና ለማህብረሰቡንም በቂ ግንዛቤ መፈጠሩንም ገልፀዋል።
ህፃናትን በጨቅላነት ከሚጠቃ በሽታ ለመታደግ የፖሊዮ ክትባት ማስፈለጉንና የመንግስታችን የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ታምራት አሰፋ አብራርቷል።
ኃላፊዉም አክሎ ዞን በአራት ቀናት ዉስጥ 74365 ህፃናቶችን ለማስከተብ ዕቅድ መያዙንም ገልፀዋል።
የደቡብ ኦሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ታደሴ ጋልጳክ በበኩሉም የፖሊዮ ስራ ዛሬ የተጀመረ ስራ ሳይሆን ከዚህ በፊትም የሀገር መንግስታችን የትኩረት አቅጣጫ እንደሆነም ጠቁመዋል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ የሚወለዱ ህፃናቶች በግዜ አስፈላጊዉን የፖሊዮ ክትባት ባለማግነታቸዉ ለተለያዩ በሽታ እየተዳረጉ መሆኑንም በማንሳት ወላጆች ልጆቻቸዉን የማስከተብ ግዴታ እንዳለባቸዉና ህፃናቶቹም የመከተብ መብት እንዳለባቸዉም አስመሮበታል።
ከዘመቻዉ ጎን ለጎን የወባ በሽታ የመከላከያ መንገዶችን በማዘወተር በትኩረት የአሰሳ ስራዉን እንድታጠናከሩ አጽንኦት ሰተዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ም/ኃላፊና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አጉነ አሾሌ በበኩሉም ይህን ዘመቻ ግብ ለማሳካት 1.4 ሚሊዮን በላይ ህፃናቶችን ለማስከተብ ግብ መነደፉን የገለፁት ስሆን ክትባቱም ከ5 ዓመት በታች በክልላችን ለሚገኙ ለሁሉም ህፃናት እንደሚሰጥም ገለፃ አድርገዋል።
ከዘመቻዉ ጎን ለጎን የወባ በሽታ ማዝመትን ለመግታት ባለድርሻ አካላት በልዩ ትኩረት መስራት እንዳለበትም አስገንዝበዋል።
የእጅ/የእግር ልፍስፍ (የፖሊዮ በሽተኞች ካሉ የመለየት እንድሁም ሁሉም ህብረተሰብ አንድም ህፃናት ሳያስቀሩ ለማስከተብ ኃላፊነትን ከአደራ ጋር ጭምር እንድትወስዱም አሳስበዋል።
በመርሃ-ግብሩም የክልል ጤና ቢሮ ፣የዞን ጤና መምሪያ ፣የማሌ ወረዳ ፊት አመራሮችና የጤና ዘርፊ አመራሮች ተሳትፈዋል።
The second round of integrated regional polio vaccination campaign started program.
South Ethiopian regional government health bureau second round polio vaccination campaign launching program has been officially started in South Omo zone, Male woreda at Koibe center.
Malee Woreda General Administrator Mr. Algaga Balancee has been at the place and has given a welcome message to the guests. He has also pointed out that polio campaign is taking place in our country and in the world to prevent the disease.
They have stated that they are planning to vaccinate 21,000 children in the district to achieve this campaign and that they have created enough awareness for the society.
South Omo zone health department head Mr. Tamrat Asefa has explained that polio vaccination is needed to save children from infant diseases and that it is the direction of our government’s attention.
The leader also stated that he has planned to vaccinate 74365 children in Aklo zone within four days.
South Omo zone prosperity party head office and government secretary Mr. Tadessie Galvak has pointed out that polio work is not a work that started today but it is also a direction of our government’s focus before.
It has also been pointed out that children born in connection with this are being exposed to different diseases because they are not getting the necessary polio vaccination on time. Parents have to vaccinate their children and that the children have the right to vaccinate.
Along with the campaign, they have emphasized to strengthen the survey by regularly deploying the prevention methods of malaria.
The deputy head of the Southern Ethiopia Regional Health Bureau and the General Director of the Public Health Institute Mr. Agune Ashole has stated that the goal of this campaign is to vaccinate more than 1.4 million children and the vaccination will be given to all children under the age of 5 in our region.
Along with the campaign, the stakeholders have also realized that to prevent the spread of malaria should work with special attention.
Hand/foot laziness (differentiate from polio patients) and also urged all the society to take responsibility with the trustee to vaccinate without leaving any child behind.
Regional health bureau, zone health department, Male woreda front leaders and health sector leaders have participated.