ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ከጤና ተቋማት አመራሮችና ባለሞያዎች ጋር በመወያየት ላይ ይገኛሉ
ክልሉ በማህበራዊ ልማት ዘርፍ ልዩ ትኩረት ከሰጣቸው ዘርፎች ጤና ዋነኛው ሲሆን፤ በዘርፉ ለጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ትኩረት በመስጠት በጤና ተቋማት ግንባታ፤ በጤና መድህን እንዲሁም በህብረተሰብ ጤና በርካታ ስራዎችን በመስራት አበረታች ውጤት ማስመዝገብ ችሏል፡፡
የክልሉ መንግስት የጤና አገልግሎት ሽፋንን ከማሳደግ ባለፈ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በማድረግ ላይ ባለው ጥረት በየደረጃው ያሉ የጤና ባለሞያዎችና የጤና ተቋማት አመራሮች የማይተካ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ፡፡
በክልሉ ከመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጀምሮ እስከ አጠቃላይ ሆስፒታል ድረስ 305 አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን ጨምሮ 287 ጤና ጣቢያዎች እና ከ 1300 በላይ ጤና ኬላዎች ሲኖሩ፤ ለህብረተሰቡ በሁሉም ተቋማት ያለምንም መስተጓጎል ተገቢው የጤና አገልግሎት በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
በመድረኩ በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች፤ የጤናው ዘርፍ አርበኝነት ለሀገር ዕድገት ባለው ሚናና በዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ በሚታዮ ችግሮች እንዲሁም በጤና ባለሙያዎች ጥያቄዎች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
President Tilahun Kebede is discussing with health institutions leaders and professionals.President Tilahun Kebede with health professionals and leaders from health institutions in the region “Patriotism of the health sector for the development of the country! They are discussing in Wolayta Sodo city with a leader’s idea.Health is one of the areas that the region has given special attention in the field of social development; in the sector, it has achieved a positive result by giving attention to the quality and access of health services, building health facilities, health insurance and public health.Health professionals and health institution leaders at all levels are playing an irreplaceable role in the regional government not only increasing health care coverage but also making quality health care accessible to the society.There are 287 health centers and more than 1300 health centers in the region starting from primary hospital to general hospital, including 305 facilities and more than 3000 health centers, the society is being provided with proper health services in all institutions without interference.It is expected that a fruitful discussion will be held on the stage regarding current regional and national issues, the role of patriotism in the health sector in the development of the country and the problems that appear in the service sector and the questions of health professionals.