የክልሉ መንግስት በ20 ሚሊዮን ብር ወጪ ባለፉት 9 ወራት 18 የጤና ተቋማት የሶላር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉ ተገለፀ
ከ2 ሚሊዮን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የወባ በሽታ ምርመራ እንደተደረገላቸውም የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ በተያዘው በጀት ዓመት በክልሉ የወባ በሽታ ወረርሽኝ መከሰቱ ለጤናው ሴክተር አገልግሎት አሰጣጥ ተግዳሮት እንደሆነ አስታውሰዋል።
በክልሉ ባለፉት 9 ወራት ከ2 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የወባ በሽታ ምርመራ ተደርጎላቸዋል ያሉት የቢሮው ኃላፊ 750 ሺህ የሚጠጉት በሽታው እንደተገኘባቸውም ጠቁመዋል ።
በበሽታው ከተጠቁ 99 በመቶ የሚሆኑት የተመላላሽ ህክምና አገልግሎት ያገኙ ሲሆን 1 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ተኝተው መታከማቸውም ተገልጿል።
የወባ በሽታ ወረርሽኝ ለመከላከል ህብረተሰቡን በማሳተፍ የተሰሩ የመከላከል ስራዎች ውጤት ማምጣታቸውን የገለፁት አቶ እንዳሻው ከመድሃኒት አቅርቦት ጋር ተያይዞ የጤና ሚኒስቴር ላደረገው ድጋፍም አመስግነዋል።
በክትትልና ቁጥጥር ዘርፍ በተከናወነ ተግባር ከ67 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት በህገ ወጥ መንገድ የገቡ የጥራት ደረጃቸው ያልተረጋገጡ መድሃኒቶችን መያዝ መቻሉን ያመለከቱት ኃላፊው ህብረተሰቡ በጤና ባለሙያዎች የሚታዘዙ መድሃኒቶችን ከህጋዊ ፋርማሲዎች እንዲገዙም አሳስበዋል።
በክልሉ ገጠር አከባቢዎች የሚገኙ የጤና ተቋማት የመብራትና የውሃ ችግር እንደሚስተዋልባቸው የገለፁት አቶ እንዳሻው ባለፉት 9 ወራት የክልሉ መንግስት በ20 ሚሊዮን ብር ወጪ 18 የጤና ተቋማት የሶላር ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችሏል ብለዋል።
It is reported that the regional government has allowed 18 health institutions to use solar in the last 9 months with the expense of 20 million birr.
The regional health bureau stated that more than 2 million people have been tested for malaria.
The head of the regional health bureau Mr. Endashaw Shibru has reminded that the epidemic of epidemic in the region in the budget year is a challenge for the health sector.
The head of the bureau said that more than 2 million communities have been tested for malaria in the last 9 months in the region has also stated that 750 thousand have been diagnosed with the disease.
99 percent of those infected with the disease have received walk-in treatment and 1 percent have been treated while sleeping.
Mr. Endashaw, who said that the preventive measures done by engaging the society to prevent the malaria epidemic, has also thanked the Ministry of Health for the support he has given in relation to the supply of medicines.
In an action carried out in the field of monitoring and control, the official has stated that more than 67 million birr illegally seized medicines that are not verified of their quality, the public has also urged to buy medicines that are prescribed by health professionals from legal pharmacies.
Mr. Endashaw who said that health institutions in the rural areas of the region are facing problems of electricity and water, said that in the past 9 months the regional government has enabled 18 health institutions to use solar at the expense of 20 million birr.