በደቡብ ኦሞ ዞን የጤና ባለሙያዎች ውይይት ተጀመረ

የውይይት መድረኩ “የጤናው ዘርፍ አርበኝነት ለአገር አንድነት” በሚል መሪ ቃል የጤና ባለሙያዎችና ሠራተኞች በተገኙበት በደቡብ ኦሞ ዞን ዲመካ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ታምራት አሰፋ የእለቱን ፕሮግራም አስመልክቶ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።
የደቡብ ኦሞ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ እና የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ጋልጶክ በበኩላቸው የጤና ባለሙያዎች ከራሳቸው በላይ የማህበረሰቡን ችግር በማስቀደም ለመፍታት እና ህይወት ለመታደግ እየሰሩ ይገኛሉ።
ይህንን እንደ ክልልና ዞን እንረዳለን ሲሉ ገልፀው የዛሬው ፕሮግራም የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ተቀራርበን በመወያየት እንድንፈታ ይረዳ ዘንድ እንደሆነ ገልፀዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር አቶ አጉኔ አሾሌ ከለውጡ ማግስት በአገራችን በርካታ ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛል፤ በጤና አገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ የእናቶችና ህፃናት ሞት ቀንሷል ክትባት በሰፊው እየተሰጠ ይገኛል።
እንዲሁም ማህበረሰቡ ወደ ጤና ተቋማት መጥተው አገልግሎት ማግኘት ጀምረዋል ፤ይህም ለውጥ የጤና ባለሙያዎች ጥረት መሆኑን አንስተዋል።
በቅርቡ የተነሱ ጥያቄዎችን :–ነፃ የባለሙያ ህክምና፣ የመኖሪያ ቤት ፣ዲውቲ ክፍያና ደመወዝ ጉዳይ ላይ ውይይት በማድረግ መንግስት ደረጃ በደረጃ የሚፈታ ይሆናል ብለዋል።
A discussion of health professionals has started in South Omo zone.
The discussion forum is under the theme “Patriotism of the health sector for the unity of the country” in South Omo zone Dimeka city with the presence of health professionals and workers.
South Omo zone health department head Mr. Tamrat Assefa has conveyed his welcome message regarding today’s program.
South Omo zone government secretary general and prosperity party head office Mr. Tadesse Galvak are working to solve the problems of the society above themselves and save lives.
He stated that they will understand this as a region and zone. Today’s program is to help us solve the problems of good governance by coming closer and discussing.
The director of the Southern Ethiopia Regional Health Bureau Public Health Institute Mr. Agune Ashole, many results are being recorded in our country the day after the change. The death of mothers and children in the field of health services has decreased and vaccination is being widely distributed.
Also the society has come to health institutions and started to get services; they have noted that this change is the effort of health professionals.
The questions raised recently:– free professional treatment, housing, duty payment and salary will be solved step by step by step by discussion.