የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ቢሮ ጋር በመተባበር 19ኛ ሳምንት የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል ግምገማ ማካሄዱን አስታዉቋል፡፡
በዉይይት መድረኩ በትኩረት ከተገምገሙ ነጥቦች ሲንመለከት የወባ መከላከልና የቁጥጥር ተግባራት፤ የስርዓተ-ምግብ እጥረት ልየታና ህክምና ፣የተቀናጀ የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ ያለበት ደረጃ፣ የእናቶችና ጨቅላ ህጻናት ሞት ቅኝት እና ሌሎች በዝርዝር የተገመገመ ሲሆን ተግዳሮቶችን በመለየት የመፍትሔ አቅጣጫ ተመላክቶበታል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ም/ኃላፊና የፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፍ አቶ መና መኩሪያ እንደገለጹት የወባ በሽታ ስርጭት ከመከላከልና ከመቆጣጠር አኳያ ማህብረሰቡን በማነቃነቅ፣ መጠነ ሰፊ የመከላከል እና መቆጣጠር ተግባራት ማከናወን እንደሚገባ እና የወባ መከላከል ተገባራትን የተቀናጀ የክፉኝ ዘመቻ ጋር በደንብ ተቀናጅቶ መሰራት እንዳለበት አሳሰቧል፡፡
አቶ መና አያይዘውም የእናቶችና የጨቅላ ህጻናት ሞትን ቅኝትና ምላሽ ተግባራትን በተመለከተ፣ መዋቅሮች በጊዜ የተከሰተውን ሞት ማሳወቅ ፣ የሞት ምክንያት ኦድት አድርጎ ቀጣይ የማስተካከያ እርምጃ መዉሰድ ላይ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው አጽናኦት ሰጥተዋል ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አጉኔ አሾሌ የወባ በሽታን ስርጭት ለመቆጣጠር እና ለመከላከል ማህብረሰብ በማሳተፍ የሚከናወነው የአከባቢ ቁጥጥር ሥራ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው አንስተው፤ የማህብረሰብ ባለቤትነት መፍጠር ወሳኝ እንደሆነና በልዩ ትኩረት በቅንጅት መሰራት እንዳለበት በአጽንኦት አንስተዋል።
በተጨማሪም ዋና ዳይሬክተሩ የወባ በሽታ መከላከል እና ቁጥጥር ሥራዎች ከአገራዊ የተቀናጀ የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ ጋር በደንብ ተቀናጅቶ መሰራት እንዳለበትም አሳስበዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ምንተስኖት መልካ ባስተላለፉት መልዕክት በጤናው ሴክተር የሚከናወኑ ተግባራት በዋናነት የማህበረሰቡን የጤና ባለቤትነት በማጎልበት በሰዉ ሰራሽና በተፈጥሮ ክስቶች ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉትን አደጋዎች ለመቀነስና ለመከላከል የሕብረተሰቡን አሳታፊነት ማረጋገጥ ተገቢነቱ የላቀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አቶ ምንተስኖት አያይዘዉ የወባ በሽታ ስርጭትን መከላከል መቆጣጠር ተግባራትን በማጠናከር ወረርሽኙ በሕብረተሰቡ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ጫና ለመቀነስ በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ በማሳሰብ በተለይ ከተማ አከባቢዎች ላይ እየጨመረ መሆኑን በመግልጽ መንስኤ በመለየት ልዩ ትኩረት በመስጠት በቅንጅት መሰራት እንዳለበት አሳስቧል፡፡
በመጨረሻም በሳምንቱ ሊከናወኑ በሚገባቸው ተግባሮች ላይ የድርጊት መርሃ ግብር በማውጣት እና ለየዘርፉ የክንውን ሃላፊነት በመስጠት የዕለቱ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከል ዉይይት ተጠናቋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ጂንካ
The Southern Ethiopia Region Institute of Public Health in cooperation with the Health Bureau announced that it has conducted the 19th week of Public Health Emergency Management Center.
The points that were carefully reviewed in the discussion stage are the functions of pest control and prevention, the identification and treatment of malnutrition, the level of an integrated measles vaccination campaign, the reconciliation of maternal and infant deaths and others were reviewed in detail.
The deputy head of the Southern Ethiopia Regional Health Bureau and the head of programs, Mr. Mena Mekuria stated that the Akaya community should be carried out a wide range of prevention and control measures and the prevention of pestilence should be done in line with the organized campaign.
Mr. Mena Ayayzewum has emphasized that the structures should report the death of mothers and infants on time, audit the cause of death and focus on taking the next corrective measures.
Mr. Agune Ashole, the director of the Southern Ethiopian Regional Institute of Public Health, has emphasized that the environmental control work that is being done by engaging the community in controlling and preventing the spread of epidemic diseases has a significant role. It is important to create community ownership and it should be done in coordination with special attention.
In addition, the director general stressed that pest control and prevention activities should be done in line with the national integrated measles vaccination campaign.
In the message of the Southern Ethiopian Regional Institute of Public Health, Mr. Mentesnot Melka, the activities that are done in the health sector are to strengthen the health ownership of the society and to reduce and prevent the risks that can happen due to man-made and natural events and ensure the participation of the society is more appropriate.
Mr. Mintesnot Ayayizew has emphasized that it should work in harmony to reduce the pressure that the epidemic may cause on the society especially in the city areas, identifying the causes and paying special attention to it.
Finally, the discussion of the day has been concluded by making an action schedule on the activities that should be done during the week and giving responsibility for the events in the sector.
Southern Ethiopia Region Institute of Public Health
ጂнка