የመረጃ አያያዝ ስርዓትን ለማዘመን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለዉሳነ ለመጠቀም የህብረተሰብ ጤና መረጃ ዲጂታላይዝ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ::
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከኢትጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የሕብረተሰብ ጤና መረጃ አያያዝ ሥርዓትን ለማዘመን ለPHEM ባለሙያዎች የPHEM-DHIS2 ስልጠና በአርባምንጭ ከተማ እየሰጠ ይገኛል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አጉኔ አሾሌ እንደገለፁት እንስቲትዩቱ የሕብረተሰብ ጤና መረጃ አያያዝ ሥርዓትን ለማዘመን ዘርፈብዙ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን በመግለፅ በክልሉ በሁሉም ዞኖች፣ወረዳዎች እና ጤና ተቋማት ዲጅታላይዝድ የሕብረተሰብ ጤና የመረጃ አያያዝ ሥርዓትን ለመዘርጋት የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጹዋል፡፡
ዋና ዳይረክተሩ አያይዘዉም የሕብረተሰብ ጤና መረጃ ሙሉነትና ወቅታዊነት ይበልጥ ለማጠናከርና መረጃዎችን ለዉሳነ ለመጠቀም የህብረተሰብ ጤና መረጃ ዲጂታላይዝድ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል፡፡
ስልጠናዉ በሶስት ዙር የሚሰጥ ሲሆን ከ12ቱም ዞን መዋቅር፣ከወረዳዎች/ከተማ አስተዳደሮች እና ጤና ተቋማት የተወጣጡ በዘርፉ የሚሰሩ ባለሙያዎች እንደሚሳተፉ ከስፍራዉ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡