የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መልካሙ አብቴ የተመራ ልዑክ አርባምንጭ ከተማ ገብቷል።
ልዕኩ አርባምንጭ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስደርስ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳሪክተር አቶ አጉኔ አሾሌ፣የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመድኃኒት ምግብና ምግብ ነክ ጉዳዮች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ዋና ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ሶንቆ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ምንተስኖት መልካን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሞያዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ልዑኩ በቆይታቸው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ተግባራት እንዲሁም የህብረተሰብ ጤና ላቦራቶሪ ያሉበትን ደረጃ የሚጎበኝ ይሆናል።
A delegation led by Dr. Melkamu Abate, Deputy Director General of Ethiopian Public Health Institute has arrived in Arbaminch.
A delegation led by Dr. Melkamu Abte, Deputy Director General of Ethiopian Public Health Institute has arrived in Arbaminch.When the delegation arrived at Arbaminch International Airport, the head of the Southern Ethiopia Regional Health Bureau Mr. Endashaw Shibru, the director of the Southern Ethiopia Public Health Institute Mr. Agune Ashole, the Southern Ethiopia Regional Medical and Food related Authority General Manager Mr. Yosef Sonko, the Southern Ethiopia Region Public Health Institute Deputy Director General Mr. Mintesnot Melka has been welcomed by senior officials and professionals.