አንድ ጤና ዙሪያ ስልጠና መሰጠቱን ኢንስቲትዩቱ ገለፀ
ኢንስቲትዩቱ አንድ ጤና ከሚመለከታቸው ተቋማት የተውጣጡ አካላት በተገኙበት ከአንድ ጤና ጋር በተያያዘ በጂንካ ከተማ ምክክር አድርጓል።
በመድረኩ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች፣ የተላመዱና በተለያየ ጊዜ የሚከሰቱ ተላላፊ በሽታዎችና መሰል ጉዳዩች ዙሪያ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት በተሳታፊዎች ተደርጓል።
ከዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ጋር በተያያዘም ገለፃ ተደርጓል።
የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ በክልላች ባይከሰትም የቅኝት ሥራው ተጠናክሮ እንደቀጠለ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ገልፀዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አጉኔ አሾሌ አያይዘው እንደገለፁት፤ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ዋና ዓላማ በየአካባቢው በተለያየ መንገድ የሚከሰቱ ተላላፊ በሽታዎችን በአንድ አሀድ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ታስቦ ነው።
በተለይ ከእንስሳት ወደ ሰው እንዲሁም በተለያየ መልኩ እንስሳት ላይም የሚከተሰቱ በሽታዎችንም መከላከል ያስችል ዘንድ ከጤና ባለሙያዎች በተጨማሪ ከእንስሳትና ዓሳ ሀብት፣ ከደንና አካባቢ ጥበቃ እንዲሁም ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ካላቸው ሴክተር መሥሪያ ቤት የተውጣጡ አካላት በተገኙበት ግንዛቤ መፈጠሩንም ኃላፊው አስረድተዋል።
ኢንስቲትዩቱ ከመቸውም ጊዜ በላይ ለዜጎች ጤናና ደህንነት ቅድሚያ ሰጥቶ እየሠራ ስለመሆኑም አቶ አጉኔ ገልፀዋል።
በመድረኩ የተገኙ አካላትም በተወያዩትና በተስማሙት ልክ ወደመጡበት አካባቢ ሲመለሱ እንደሚሠሩ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
The institute stated that one health training has been given.
The Southern Ethiopian Institute of Public Health has stated that communicable diseases that affect the health of citizens should be continuously prevented by collaborating with stakeholders.The institute has held a consultation in Jinka city with members from concerned institutions.On the stage, a document was presented and discussed with the participants about diseases that are transmitted from animals to humans, common and frequently occurring diseases and similar issues.A statement has been made regarding the disease of monkey pox.The director of the institute stated that the colonial work has continued even though the disease of monkey pox is not occurring in the region.As stated by Mr. Agune Ashole, the director general of the Institute of Public Health of Southern Ethiopia Region, the main purpose of the awareness raising platform is to prevent and control communicable diseases that occur in different ways in the region.In order to prevent diseases from animals to humans, in addition to health experts from animal and fish resources, forest and environment protection and other sectors related to the issue, the official explained that awareness has been created.Mr. Agune has stated that the institute is working with priority for the health and safety of citizens more than ever.Those who were present on the stage also gave their opinion that they will work when they return to the place they came from as they discussed and agreed.