The Southern Ethiopia Region Institute of Public Health in cooperation with the Health Bureau has announced that it has held the 22nd week of Public Health Emergency Management Center.Looking at the points raised in the discussion stage; the report of diseases that will be reviewed during the week; the report of deaths of mothers and infants and response activities; the situation of monkey pox disease and the preparation of health institutions; the spread of plague; the summary report of the coordinated polio campaign and some of the best experiences taken were reviewed; An action plan is set on identifying the challenges and solving them.Southern Ethiopia Regional Health Bureau, Public Health Institute vice director Mr. Mintesnot Melka stated that in the second round of polio vaccination campaign more than 1.5 million (108%) children under 5 years have been vaccinated and the campaign was successful and thanked all the stakeholders who participated in every step and shared the good experiences gained in the campaign through regular activities. He insisted that he should continue.Mr. Mentesnot pointed out that in areas where food shortage is high, it is necessary to respond quickly and work in harmony with other sectors.Aklewum M Pox (MPox) disease is being done with special attention in the region; they have confirmed that there is no confirmed case (patients) found as a region.In addition, the specialists who can take samples and diagnose suspected patients have taken proper training and are ready. In addition, four regions centers (Arba Minch General Hospital, Wolayta Sodo Teaching Hospital, Dila General Hospital and Jinka General Hospital) have stated that they are ready to treat confirmed patients.Realizing that the disease is transmitted when it is close contact with a sick person, they have asked the society to take necessary precautions.Mr. Nebiyu Beza, the head of the health bureau and the administration and finance sector, stated that the work done to control the measles epidemic as a region is admirable and emphasized that the work of coordination should be strengthened in all areas.Mr. Nebiyu Ayayzewum stated that the epidemic situation still needs special attention and said that prevention and response activities should be continued by involving all stakeholders where the society is.Regarding the death of infants, it has been evaluated that it is necessary to go into service delivery in some structures and formulate a team. It has also been noted that reporting and auditing at every step should be done to prevent similar deaths or deaths.Finally, the discussion of the day has been concluded by making an action schedule on the activities that should be done during the week and giving responsibility for the events of the sector.Southern Ethiopia Regional Health Bureau Public Health Instituteንካнка
በዉይይት መድረኩ በትኩረት ከተነሱት ነጥቦች ስንመለከት ፤ በሳምንቱ ዉስጥ ቅኝትና አሰሳ የሚደረግባቸው የበሽታዎች ሪፖርት፤ የእናቶችና የጨቅላ ህጻናት ሞት ሪፖርትና የምላሽ ተግባራት ፤ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ሁኔታና የጤና ተቋማት ዝግጅት ሁኔታ ፤ የወባ በሽታ ስርጭትና ለመቆጣጠር የተሰሩ ተግባራት ፤ የተቀናጀ የፖሊዮ ዘመቻ ማጠቃለያ ሪፖርት እና የተወሰዱ ምርጥ ተሞክሮዎች የተገመገሙ ስሆን ፤ ተግዳሮቶችን በመለየት በመፍትሔ ላይ የድርጊት መርሐግብር ተቀምጧል ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ምንተስኖት መልካ እንደገለጹት በሁልተኛ ዙር በተቀናጀ ፖሊዮ ክትባት ዘመቻ እንደክልል ከ1.5 ሚልዮን በላይ(108%) ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ክትባት ማግኘታቸውንና ዘመቻው በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን በመግለጽ በየደረጃዉ ለተሳተፉ ባለድርሻ አካላት ምሰጋና በማቅረብ በዘመቻ ስራ ላይ የተገኘዉን መልካም ተሞክሮችን በመደበኛ ተግባራት ላይ ማስቀጠል እንደሚገባ አሳሰበዋል፡፡
የሥርዓተ ምግብ አጥረት ከፍ ባለባቸው አከባቢዎች ፈጥኖ ምላሽ መስጠት እና ከሌሎች ሴክተር ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ አቶ ምንተስኖት አንስተዋል ።
አክለውም ኤም ፖክስ (MPox) በሽታ በልዩ ትኩረት ቅኝትና አሰሳ በሁሉም ክልሉ አከባቢ እየተሰራ መሆኑን አንስተው ፤ እንደ ክልል እስከአሁን የተረጋገጠ ኬዝ(ህሙማን ) እንዳልተገኘ አረጋግጠዋል ።
በተጨማሪም በበሽታው ከተጠረጠሩ ህሙማን ናሙና መዉሰድ እና ምርመራ ማድረግ የሚችሉ ባለሙያዎች ተገቢውን ስልጠና ወስደው ዝግጁ መሆናቸውን አንስተዋል ። በተጨማሪም የተረጋገጠ ህሙማን ቢገኝ ለይቶ ለማከም እንዲቻል እንደ ክልል አራት ማዕከላት ( አርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል፥ ወላይታ ሶዶ ማስተማሪያ ሆስፒታል ፣ ዲላ አጠቃላይ ሆስፒታል እና ጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ) ዝግጁ መሆናቸውን አንስተዋል ።
በሽታዉ ከታመመ ሰዉ ጋራ የቅርብ ንክኪ ስኖር የሚተላለፍ መሆኑን በመገንዘብ ህብረተሰብ አስፈላጊዉን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
የጤና ቢሮ ም/ቢሮ እና የአስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነብዩ ቤዛ በበኩላቸዉ እንደክልል የኩፍኝ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር የተሠራው ሥራ የሚደነቅ መሆኑን በመግልጽ አሁንም የቅኝት ሥራ በሁሉም አከባቢ መጠናከር እንዳለበት በአጽንኦት ተነስቷል ።
አቶ ነብዩ አያይዘዉም ወባ በሽታ ሁኔታ አሁንም ልዩ ትኩሬት የሚሻ መሆኑን በመግለጽ የመከላከልና ምላሽ ተግባራት ሁሉን ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መለክ ማህበረሰቡ ባለበት በማድረግ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
የጨቅላ ህጻናት ሞት በሚመለከት፤ በእንዳንድ መዋቅሮች የአገልግሎት አሰጣጥ ጭምር ገባ ብሎ ቲም በማዋቀር ማየት እንደሚያስፈልግም የተገመገመ ስሆን ፤ ሪፖርት ማድረግና በየደረጃው ኦድት አድረገው ተመሳሳይ ሞት ወይም ማስቀረት የምንችለው ሞት እንዳይከሰት አጠናክረው መስራት እንዳለበትም አሳስበዋል ።
በመጨረሻም በሳምንቱ ሊከናወኑ በሚገባቸው ተግባሮች ላይ የድርጊት መርሃ ግብር በማውጣት እና ለየዘርፉ የክንውን ሃላፊነት በመስጠት የዕለቱ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከል ዉይይት ተጠናቋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ጂንካ