In the second round of polio vaccination campaign in southern Ethiopia region the first day of implementation has been reviewed online.
The situation of the vaccination launching program held at each level, the supply and distribution of vaccines, the situation of coordinated activities, and the implementation of vaccination teams and various issues and solutions of the campaign were discussed.
Deputy head of the regional health bureau and the director of the Institute of Public health Mr. Agune Ashole in his message the launching program that was held in every stage on the first day of the campaign, in all areas of our region, the results were encouraging.
The Director General does not hold back. He stated that in the campaign more than 1.4 million children under the age of 5 will benefit from the service. He stressed that all the authorities should do their part to deliver the vaccination to every parent in a high quality manner.
Activities to be done in conjunction with the campaign i.e. making children under the age of 5 who have not been vaccinated and have stopped vaccinated in the regular vaccination program; identifying mothers with urinary tract problems (fistula) related to childbirth and sending them to medical facilities; strengthening malaria prevention and control activities and M-pox epidemic. They have emphasized that reconciliation and survey works should be done in all structures.
The regional health bureau management members, supporting professionals, the heads of the zone health department and different stakeholders have participated in the discussion.
Southern Ethiopia Region Institute of Public Health
#JINKA
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሁለተኛ ዙር የተቀናጀ ፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ተግባራት ትግበራ ሁኔታ የመጀመሪያው ቀን አፈጻጸም በበይነ መረብ ተገምግሟል።
በየደረጃው የተካሔደዉ የክትባት ማስጀመሪያ መርሀግብር ሁኔታ(launching)፣ የክትባት አቅርቦት እና ስርጭት፣ተቀናጅቶ የሚስሩ ስራዎች አትገባበር ሁኔታ፣ እንዲሁም የክትባት ቡድኖችን አፈጻጸም ጨምሮ የተለያዩ ጉዳዮች እና ዘመቻው ያጋጠሙ ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው ተወያይተዋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ም/ኃላፊ እና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አጉኔ አሾሌ በመልዕክታቸው በዘመቻው የመጀመሪያ ቀን በየደረጃው የተካሄደዉ ማስጀመሪያ መርሀግብር ፣በክልላችን ዉሰጥ ባሉ በሁሉም አከባቢዎች ዘመቻዉ በመጀመርያ ቀን መጀመሩ እና የተገኘው ውጤት አበረታች መሆኑን ገልጿል።
ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም በዘመቻው ከ1.4 ሚሊዮን በላይ እድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልፀው ሁሉም ባለድሻ አካላት ክትባቱን ለእያንዳነዱ ታላሚ ህፃን ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ለማዳረስ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ከዘመቻው ጋር ተቀናጅቶ የሚስሩ ተግባራት ማለትም ፣በመደበኛው የክትባት መርሀ-ግብር ክትባት ሳይወስዱ የቀሩና ጀምረው ያቋረጡ እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት የክትባት አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ፣ከወሊድ ጋር በተያያዘ የሽንትና የሰገራ መቆጣጠር ችግር (ፊስቱላ) የገጠማቸውን እናቶች መለየት እና ወደ ህክምና ተቋም መላክ ፣የወባ በሽታ መከላከል እና ቁጥጥር ሥራዎችን ማጠናከር እና የM-pox ወረርሽኝ ቅኝትና አሰሳ ሥራዎች በሁሉም መዋቅር ተቀናጅቶ መከናወን እንድሚገባም አጽናኦት ሰጥተዋል፡፡
ዉይይቱ ላይ የክልሉ ጤና ቢሮ ማናጅሜንት አባላት፣ደጋፍ ባለሙያዎቸ፣የዞን ጤና መምሪያ ኃላፊውች እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ጂንካ